ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና የፈተናዎች ኤጀንሲ
ራዕይ፣
የላቀ የፈተናና የትምህርት ምዘና ማዕከል አስከ 2012 ዕውን ማድረግ፤
ተልዕኮ፣
የሀገሪቱን የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲና ሥርዓተ ትምህርት መሠረት ያደረጉ ሀገር አቀፍ ፈተናዎች የማዘጋጀትና የማስተዳደር፣ የውጤት
ማረጋገጫና የድጋሚ ምስክር ወረቀት መስጠት፣ በመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን የመመደብና፣ የትምህርት ብቃት ምዘና
ጥናትና ምርምር በማካሄድ ለባለድርሻ አካላት ግበረ መልስ በመስጠት ተቋማዊ ተግባሩን ይወጣል፡፡
እሴቶች/የአሰራር ፍልስፍናዎች/
- ለፈተናና ምዘና ጥራት ቅድሚያ እንሰጣለን
- ፈጠራንና ችግር ፈቺነትን እናጠናክራለን
- በጥናትና ምርምር የቅበላና የምዘና ችግሮቻችንን እንፈታለን
- በእውቀትና በእምነት እንመራለን
- ግልፅነትና ተጠያቂነት እናሰፍናለን
- ለለውጥ ዝግጁ በመሆን፣ የመግባባትና የመቻቻል ባህል እናጎለብታለን
- ለተገልጋይ ተደራሽ የሆነ አገልግሎት እንሰጣለን
- በጋራ መሥራት መገለጫችን ነው
- አሳታፊነትና ፍትሐዊነት እናሰፍናለን