የሁለተኛ
ደረጃ መልቀቂያ ፈተና በኢትዮጵያ በሙከራ መልክ መቅረብ የጀመረው በ1938 ዓ.ም ሲሆን ለከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ማገልገል የጀመረው
ግን የቀድሞው ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ትምህርት ሚኒስቴርን በመወከል የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ጽ/ቤት በ1942 ዓ.ም ካቋቋመ በኋላ
ነው ። እነዚህ ላይ መታወስ የሚገባው ከ1947 ዓ.ም. በፊት
ማንኛውም ተማሪ ከፍተኛ ትምህርት ቤት ለመግባት በተጨማሪ በእንግሊዝ አገር የሚዘጋጀውን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን (General
Certificate of Education) ወስዶ ማለፍ ግዴታው ነበር። የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና በዕድገት በኅብረት ዘመቻ
ምክንያት ብቻ ለሁለት ዓመት (1967ዓ.ም እና 1968 ዓም) ሳይሰጥ ከመቅረቱ በስተቀር የተቋረጠበት ጊዜ አልነበረም።
ጽ/ቤቱ
እንደ ተቋቋመና ከዚያም በኋላ ለጥቂት ዓመታት የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተናን በየአመቱ የወሰዱት ተፈታኞች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ
እየጨመረ ቢሄድም የተፈታኝ ቁጥር እጅግ አነስተኛ ስለ ነበር
ፈተናውን ለማዘጋጀት ያስፈልግ የነበረው የሰው ኃይል የገንዘብ ወጪ እንዲሁም የስራው ብዛት አነሰተኛ በመሆኑ ስራውን በቀለጠፈ አኳኋን
ለማካሄድ እምብዛም አላስቸገረም ነበር ። ለምሳሌ በመጀመሪያዎቹ 9 ዓመታት ውስጥ (ማለት ከ1942 ዓ.ም እስከ 1950 ዓ.ም)የተፈታኝ
ቁጥር ከ55 እስከ 288 ሲደርስ በሚቀጥሉት 9 ዓመታት ግን (ከ1951 ዓ.ም እስከ 1959 ዓ.ም ) የተማሪ ቁጥር በየዓመቱ መጠነኛ
ጭማሪ እያደረገ በመሄዱ ከ370 እስከ 2381 ደርሷል።
ከዚያም በሚቀጥሉት ዓመታት ግን የተፈታኝ ቁጥር በየአመቱ
እየበዛ ሄዶ በ1975 ደግሞ የተፈታኙ ቁጥር ወደ 100,000
ከፍ አለ ።
አሁን
ያለንበት ደረጃ ግን ከዚያ በጣም የላቀው ከ 1993 ዓ/ም
ጀምሮ አዲስ በተቀረፀው የትምህርት ፖሊሲ መሰረት ሃገር አቀፍ ፈተናዎቹ በ10ኛ እና 12ኛ ክፍል እንዲሰጡ መደረጉ ሲሆን የ 10ኛ ክፍል ፈተና ሲጀመር 100, 000 ከነበረው የተፈታኝ
ብዛት በአሁኑ ወቅት ከ 1,000, 000 በላይ ሲደርስ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ደግሞ ከ 140,000 በላይ ደርሷል።